ታቦተ ኖኅ
👉ለምን "ታቦተ ኖኅ"⁉️
"ወተዘከሮ እግዚአብሔር ለኖኅ።" እግዚአብሔርም ኖኅን አሰበው (ዘፍ. 8፥1)
"ታቦተ ኖኅ" ብዬ የዩቱብ ቻናሌንና የሚዲያ ገጾቼን የሰየምኩት በአጋጣሚ ወይም ለውበት ብቻ አይደለም። የኖኅ መርከብ በመጽሐፍ ቅዱስ የድኅነት፣ የተስፋ፣ የመጠለያ፣ የትዕግሥትና የእግዚአብሔር ምሕረት ምልክት ናት። በዘመነ ጥፋት የሰው ልጅ ኃጢአትና ዓመፅ በምድር ላይ በበዛ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ለዓለም የድኅነት በር አዘጋጀ፤ ይህም የኖኅ መርከብ ነበረች።
"ኖኅም እግዚአብሔር እንዳዘዘው ሁሉ እንዲሁ አደረገ።" (ዘፍ. 6፥22)
ኖኅ መርከቧን የሠራው ለራሱ ብቻ አልነበረም፤ ለሌሎችም የሕይወት መንገድ እንድትሆን ነበር። በመርከቧ ውስጥ ብዙ ነፍሳት ከጥፋት ዳኑ፤ የሕይወት ዘርም ተጠበቀ።
✍️ይህንን መንፈሳዊ ሐሳብ በልቤ ይዤ "ታቦተ ኖኅ" የሚለውን ስም መረጥሁ። ምክንያቱም ዛሬ የኖኅ መርከብ በእንጨት ተሠርታ ባትኖርም፣ እግዚአብሔር ለዘመናችን የሰጠን ከዳዲስ መሣሪያዎች መካከል በቅጥነተ- ሕሊና በዓይነ-ላህም !ሳይሆን በዓይነ-ንስር ፤ ለተመለከተው#እና መልካሙ ጎዳና ላይ ለተሳፈረበት የዚህ ዘመን ታላቁ መርከብ (ታቦተ ኖኅ) አንዱ ሚዲያ ነው። ዩቱብ፣ ፌስቡክ፣ ቲክቶክ እና ሌሎች ማኅበራዊ ሚዲያዎች በአግባቡ ከተጠቀምንባቸው የእውቀት፣ የተስፋ፣ የመንፈሳዊ ሕይወትና የድኅነት መርከብ ሊሆኑ ይችላሉ።
ሚዲያ ነፍሳትን ሊያድን ይችላል!
አንድ ትምህርት የጠፋን ሰው ወደ እውነት ሊመልስ ይችላል። አንድ መንፈሳዊ መልእክት ተስፋ የቆረጠን ሰው ሊያጽናና ይችላል። አንድ ጥሩ ቪዲዮ ወጣትን ከሱስ፣ ከተስፋ መቁረጥና ከጥፋት መንገድ ሊመልስ ይችላል።
"ሂዱ ወደ ዓለም ሁሉ ፥ ወንጌልንም ለፍጥረት ሁሉ ስበኩ።" (ማር. 16፥15)
በቀድሞ ዘመን ሐዋርያት በእግር ተጉዘው ወንጌልን ያደርሱ ነበር፤ ዛሬ ግን አንድ መልእክት በጥቂት ሰከንዶች ወደ መላው ዓለም ሊደርስ ይችላል። ይህ ታላቅ ዕድል ነው።
ነገር ግን ሚዲያ በስህተት ከተጠቀምንበት ጉዳት ያመጣል!
👉ሚዲያ እንደ እሳት ናት፤ ምግብን ልታበስል ትችላለች፣ ቤትንም ልታቃጥል ትችላለች። በዛሬው ዘመን ምክንያት የሚዲያ አጠቃቀም ብዙ ችግሮች ተፈጥረዋል፦
የሐሰት መረጃ መስፋፋት
የጥላቻ ንግግር
የጊዜ ብክነት
የሥነ ምግባር መበላሸት
የቤተሰብ ግንኙነት መዳከም
የወጣቶች መንፈሳዊ ሕይወት መቀዝቀዝ
ራስን ከሌሎች ጋር በማወዳደር የሚፈጠር የሥነ ልቦና ጫና
"ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ ነገር ግን ሁሉ አይጠቅምም።" (1ኛ ቆሮ. 6፥12)
ይህ የሐዋርያው ቃል ለሚዲያም ይሠራል። ሁሉን ማየት እንችላለን፣ ሁሉን መስማት እንችላለን፣ ነገር ግን ሁሉ ለነፍሳችን አይጠቅምም።
የእኛ ጥሪ
"ታቦተ ኖኅ" ሚዲያ የተፈጠረው ለዝና፣ ለተከታዮች ብዛት ወይም ለቁጥር ብቻ አይደለም። ዓላማው ፦
✓ እውቀትን ማስፋፋት
✓ እምነትን ማጽናት
✓ ተስፋን መስጠት
✓ ነፍሳትን ማነጽ
✓ መንፈሳዊ ትምህርትን ማድረስ
✓ ሰዎችን ወደ እውነትና ወደ ክርስቶስ መምራት
"እናንተ የዓለም ብርሃን ናችሁ።" (ማቴ. 5፥14)
👉ስለዚህ ሚዲያችን የጨለማ መሣሪያ ሳይሆን የብርሃን መሣሪያ መሆን አለበት። እንደ ኖኅ መርከብ በማዕበል መካከል የሕይወት ተስፋ እንደነበረች፣ "ታቦተ ኖኅ" ሚዲያም በዚህ የዲጂታል ዘመን ውስጥ ለብዙዎች የእውነት፣ የተስፋና የድኅነት መርከብ እንድትሆን እንመኛለን እንሰራማለን ።
"✍️በኖኅ መርከብ ብዙ ነፍሳት እንደዳኑ፣ በዚህ 'ታቦተ ኖኅ' ሚዲያም ብዙዎች እውቀትን፣ እምነትን፣ ተስፋን እና ሕይወትን እንዲያገኙ ጸሎታችንና ጥረታችን ነው።"
#ታቦተ_ኖኅ #የኖኅ_መርከብ #ሚዲያ_ለድኅነት #ለእውቀት #ለእምነት #ለሕይወት #ለአገልግሎት #ለወንጌል #ብሩህ የሚያደርግ አማናዊ መጓጓዣ ነው ፈጥነው ይሻፈሩ በመርከቧ 👈
ቀን 12 /10/2018 ዓ'ም
መምህር ኤፍሬም ምናለ 🤝
- 2026
- English
- 10 (IMDb)